የኢንፌክሽን መንገዶች እና እራስዎን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ

በኤች አይ ቪ ጋር የሚሆሩ ግለሰቦች ወይም ሕሙማን እና እንደዚሁም ስኬታማ ህክምና ላይ የሚገኙ እና በደማቸው ውስጥ ተለኪያዊ የቫይረስ ቁጥር መጠን የሌላቸውን ግለሰቦች በኤች አይ ቪ ለሌሎች ማስተላለፍ አይችሉም ፡፡ ኤች አይ ቪ እንዲሁ በማኅበራዊ ግንኙነት ማለተም በመሳሳም ፣ በመተቃቀፍ ፣ አንድን ኩባያ በመጋራት ወዘተ ተላላፊ በሽታ አይደለም ፡፡

scheduleOppdatert: 22.07.2021

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ኤች አይ ቪ በዋነኝነት የሚተላለፈው ኤች አይ ቪ ካለበት እና ህክምና ላይ ከማይገኝ ሰው ጥንቃቄ የጎደለው ወሲባዊ ግኑኝነትን በመፈጸም ፣ ደም ከሌላ ሰው በማግኘት እና ከእናት ወደ ልጅዋ በእርግዝናዋ ፣ በመወለድ እና ጡት በምታጠባት ወቅቶች    ሊተላለፍ ይችላል ፡፡

ራስዎን ከኤች አይ ቪ ለመከላከል የሚያበቁ ብዙ ዘዴዎች አሉ

ስኬታማ ህክምና ፣ ኤች አይ ቪ ካለባቸው እና በተሳካ በቂ ህክምና ላይ ካሉ ሰዎች በኤች አይ ቪ የመበከል አደጋ የለውም ፡፡ ይህ ማለትም ግለሰቡ ህክምናውን ይከተላል ፣ መድሃኒቱን ይወስዳል እናም ስለሆነም የቫይረሱ ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ በሆነ መንገዱ ሲጠበቅ ለማንም ማለትም ጥበቃ በሌለው ሁኔታ በፆታዊ ግንኙነትም ሆነ በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅቶች ሊተላለፍ      የማችል ነው ፡፡

ስኬታማ ህክምና ኤች አይ ቪ ሕክምና

የኤች አይ ቪ ሕሙማን በቂ በሆነና ስኬታማ  ህክምና ላይ ካሉ ግለሰቦች ኤች አይ ቪን የመስተላለፍ አደጋ የለቸውም ፡፡ ይህ ማለትም ግለሰቡ ህክምናውን ይከተላል ፣አስፈላጊውን  መድሃኒቱን ይወስዳል እናም ስለሆነም የቫይረሱ ቁጥር እህግ በጣም ጥቂት ስለሚሆን ጥንቃቄ ባልተጠበቀበትም ፆታዊ ግንኙነትም ሆነ በእርግዝና ወይም በወሊድ በሽታው ሊተላለፍ አይችልም ማለት ነው ፡፡

 ኮንዶም በኤች አይ ቪ እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ ሌሎች የአባለዘር በሽታዎች ከመበከል የሚከላከል ሲሆን በwww.gratiskondomer.no ከሚባለው ድሕረ ገጽ ያለ መንም ወጭ ኮንዶምን ማዘዝ ይቻላል ።

ፕራይፕ (PrEP) (ቅድመ-ተጋላጭነት መከላከያ ወይም preeksponeringsprofylakse) የኤች አይ ቪ መደሐኒት ሲሆን የኤች አ ቪ ተበካይ ላልሆኑ (hivnegative) ግለሰቦችን ከኤች አቪ በሽታ መበከል የሚጠበቅ እና የመንጠቀቂያ መድሐኒት ነው።  

ፕራይፕን የሚባለውን መድሐኒት ለማኘት ከመደበኛ ሐኪምዎት ወደ ኡላፍ ተመላላሸ ሆስቲፒታል (Olafiaklinikken)  ወይም ወደ አካባቢዎ ለሚገኘው የለተላላፊ በሽታ መምርመሪያና ሕክምና በሚሰጥበት በአጥቢዎ ወደሚገኘው ሆስፒታል ሪፈራል ሊኖርዎት ብቻ ነው።

አንድ ግለሰብ ለከባድ በሽታ የመበከል የአደጋ ሁኔታ ከተጋለጠ ፣ ፒኢፒ (PEP)(ድህረ-ተጋላጭነት መከላከያ) ኤች አይ ቪ ቫይረስ ወደ ሕዋሳት እእንዳይገባ እና እንዳይባዛ የሚያግድ መድኃኒት ሊወስድ ይችላል ፡፡ ፒኢፒን (PEP)በተቻለ ፍጥነት ወዲያውኑ መውሰድ ሲያስፈልግ በተለይም  ለኤች አይ ቪ ከተጋለጡ በሁላ እስከ 48 ሰዓታት ከማለፉ በፊት መወሰድ የግድ አስፈላጊ ነው ፡፡ ፒኢፒ መድሀኒቱን ለ28 ቀናት መውሰድ ያስፈልጋል ፡፡ በኖርዌይ የሚገኙ ማንኛውም የአስቸኳይ ጊዜ ሕክምና አግልግሎት ሰጭ ተቋማት (akuttmottak) እና እንደዚሁም በማንኛውም ታላላቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የድንገተኛ ሕክምና ተቋማት (storbylegevakter) ፒኢፒንወይምPEP የተላላፊ በሽታ ልዩ ባልሙያን ሀኪም ሳያማክሩን መድሐኒቱን መስጥት ይችላሉ።

Les også

schedule22.07.2021

→ ኤች አይ ቪ እና ስል ኮቪድ- 19 (Hiv og Covid-19)

ከኤች አይ ቪ ሕሙማን በመሆን በሚኖሩበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ወይም በኳቪድ -19 መበከል ከባድ የህመም አደጋ የተጋለጡ አይደሉም ፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የበሽታ የመከላከል አቅም ካለዎት (ማለትም ከ 200 ሲዲ 4 ቆጠራዎች በታች ወይም (dvs. under 200 CD4-tall)) እና ሌሎች ተጨማሪ ከባድ በሽታዎች ከአለበዎት ግን ልመጠቃት ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት ሊኖርዎት ይችላል ፡፡

schedule22.07.2021

→ ድጋፍ የት ማግኘት ይችላል

በአጠቃላይ በኖርዌይ ውስጥ በኤች አይ ቪ ለተያዙ ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ ፡፡ ከዚህ በታች የተወሰኑት እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ በተጠቀሱት ድርጅቶች በሙሉ ልዩ ባለሙያዎችን በማግኘት ወይም ከሌሎች ኤች አይ ቪ ጋር ከሚኖሩ ገለሰቦች ጋር ለመገናኘት እድል ያገኛሉ።