የአእምሮ እና ማህበራዊ ድጋፍ

በኤች አይ ቪ ተበካይ ሕሙማን አብሮ ከበሽታው ጋር ለመኖር ከባድ ሁኒታዋች ሊያጋጥማቸው ይችላል ። ምክንያቱም በኅብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ጭፍን ጥላቻዎች መኖርና እና እንደዚሁም ስለ ኤች አይ ቪ ያለው ዕውቀት አነስተኛ በመሆኑ ምክነያት ነው ፡፡ ስለሆነም ድጋፍ ሊሰጥዎት የሚችል ሰው መኖራቸው እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡

scheduleOppdatert: 22.07.2021

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ይህም ጓደኛ ፣ ቤተሰብ ፣ ሌሎች በኤች አይ ቪ የተበከሉ ሕሙማን  ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ደግሞ ለምሳሌ  ስብሰባዎች ላይ መገኘት  ወይንም ኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge) ድርጅ መሄድ ይችላሉ ፡፡ በኢንፌክሽን በሽታ ህክምና ክፍሎች ውስጥ ያሉ ሀኪሞች እና ነርሶች ጥሩ ድጋፍ ናቸው ሆኖም ግን ከኤች አይ ቪ ጋር አብረው ከሚኖሩ ግለሰቦችን ጋር መገናኘት በእውነቱ በኤች አይ ቪ የተያዘ ህይወት እንዴት እንደሚመስል የበለጠ ግንዛቤ እና እውቀት ለማኘት ያስችላል ፡፡ የሂቪ ኖርዌ የአቻ አገልግሎት (HivNorges likepersontilbud) ለኤች አይ ቪ ሕሙማን እና ለዘመዶቻቸው ከሌሎች የኤች አይቪ ሕሙማና ቤተሰቦቻቸው ተገናኝተው ልምድንና ምክርን ለመቀያያር የሚያስችል እድሎችን የሚቀርብ ድርጅት ነው ።

Les også

schedule22.07.2021

→ ኤች አይ ቪ እና ስል ኮቪድ- 19 (Hiv og Covid-19)

ከኤች አይ ቪ ሕሙማን በመሆን በሚኖሩበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ወይም በኳቪድ -19 መበከል ከባድ የህመም አደጋ የተጋለጡ አይደሉም ፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የበሽታ የመከላከል አቅም ካለዎት (ማለትም ከ 200 ሲዲ 4 ቆጠራዎች በታች ወይም (dvs. under 200 CD4-tall)) እና ሌሎች ተጨማሪ ከባድ በሽታዎች ከአለበዎት ግን ልመጠቃት ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት ሊኖርዎት ይችላል ፡፡

schedule22.07.2021

→ ድጋፍ የት ማግኘት ይችላል

በአጠቃላይ በኖርዌይ ውስጥ በኤች አይ ቪ ለተያዙ ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ ፡፡ ከዚህ በታች የተወሰኑት እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ በተጠቀሱት ድርጅቶች በሙሉ ልዩ ባለሙያዎችን በማግኘት ወይም ከሌሎች ኤች አይ ቪ ጋር ከሚኖሩ ገለሰቦች ጋር ለመገናኘት እድል ያገኛሉ።