HivNorge

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

NYHETER

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።

schedule21.12.2021

→ በ ኡለቮል (Ullevål) ውስጥ የምክክር ላይ ለውጦች

NYHETER

በኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኡለቮል በሚገኘው ተላላፊ በሽታዎች የተመላላሽ ታካሚ ክሊኒክ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ በተከሰተው የሰው ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት የገናን ጊዜ ሙሉ ምክክር የሚደረገው በስልክ ነው። ሁሉም የደም ምርመራዎች እንደተለመደው ማድረግ ይቻላል።

schedule22.07.2021

→ ኤች አይ ቪ እና ስል ኮቪድ- 19 (Hiv og Covid-19)

ከኤች አይ ቪ ሕሙማን በመሆን በሚኖሩበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ወይም በኳቪድ -19 መበከል ከባድ የህመም አደጋ የተጋለጡ አይደሉም ፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የበሽታ የመከላከል አቅም ካለዎት (ማለትም ከ 200 ሲዲ 4 ቆጠራዎች በታች ወይም (dvs. under 200 CD4-tall)) እና ሌሎች ተጨማሪ ከባድ በሽታዎች ከአለበዎት ግን ልመጠቃት ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት ሊኖርዎት ይችላል ፡፡

schedule22.07.2021

→ ድጋፍ የት ማግኘት ይችላል

በአጠቃላይ በኖርዌይ ውስጥ በኤች አይ ቪ ለተያዙ ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ ፡፡ ከዚህ በታች የተወሰኑት እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ በተጠቀሱት ድርጅቶች በሙሉ ልዩ ባለሙያዎችን በማግኘት ወይም ከሌሎች ኤች አይ ቪ ጋር ከሚኖሩ ገለሰቦች ጋር ለመገናኘት እድል ያገኛሉ።

schedule22.07.2021

→ ኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge)

ከኤች አይ ቪ ሕመም ጋር ቀጥታ ግኑኝነት በአለው ነግሮች ላይ ሕጋዊ ጥያቄ ከአሎት ወይም የሕግ አገልግሎት ማግኘት ከአስፈለግዎች ኤች አይ ቪ ኖርዊ ሊረዳዎች ይችላል ። በተጨማሪም የአጠቃል ምክር የመስጥትን አገልግሎትን ስለምናቀርብ ከኤች አይ ቪ የተያያዙ ሌሎች ጥያቄዎች ካሉዎት በምክር ልንረዳዎች እንችላለን፡፡

schedule22.07.2021

→ መድሕን ወይም ዋስትና

መድሕን በሚገቡበት ጊዜ የጤና መረጃ እንዲያቀርቡ የሚጠይቁ አንዳንድ የመድሕን ዓይነቶች አሉ ፡፡ ከነዚህም መካከል የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድሕኖ ናቸው ፡፡

schedule22.07.2021

→ ሕግ

ከኤች አይ ቪ ጋር ለሚኖሩ ሕሙማን አንዳንድ መብቶች እና ግዴታዎች አላቸው ፡፡ በኢንፌክሽን ቁጥጥር ሕግ ደንቡ መሠረት በኖርዌይ ውስጥ ለኤች አይ ቪ ሕሙማን ሕክምናዎች በነፃ ሲኖን እንደዚሁም ከሚከፈልም የግል ክፍያም ነጻ ነው ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ለጥርስ ሕክምና የአንዳንድ ወጪዎች ተመላሽ ገንዘብም ማግኘት ይችላሉ ፡፡

schedule22.07.2021

→ የአእምሮ እና ማህበራዊ ድጋፍ

በኤች አይ ቪ ተበካይ ሕሙማን አብሮ ከበሽታው ጋር ለመኖር ከባድ ሁኒታዋች ሊያጋጥማቸው ይችላል ። ምክንያቱም በኅብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ጭፍን ጥላቻዎች መኖርና እና እንደዚሁም ስለ ኤች አይ ቪ ያለው ዕውቀት አነስተኛ በመሆኑ ምክነያት ነው ፡፡ ስለሆነም ድጋፍ ሊሰጥዎት የሚችል ሰው መኖራቸው እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡

schedule22.07.2021

→ ምርመራው ውጤቱ አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆነ

ለኤች አይ ቪ ምርመራው ውጤት አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆን ወደ ተላላፊ በሽታ የጤና ተቋም ተልከው ይሕክምና እግልግሎት እንዲያገኙ እድል ይቀርብሎታል ፡፡ ከኖርዌይ ውስጥ ከኤች አይ ቪ በሽታ ጋር ለተያዙ ህክምናዎች በሙሉ በነፃ ይሰጣሉ ፡፡

schedule22.07.2021

→ ለኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ

በኤች አይ ቪ መበከልን ለማወቅ የሚቻልበት መንገድ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው ፡፡

schedule22.07.2021

→ የኢንፌክሽን መንገዶች እና እራስዎን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ

በኤች አይ ቪ ጋር የሚሆሩ ግለሰቦች ወይም ሕሙማን እና እንደዚሁም ስኬታማ ህክምና ላይ የሚገኙ እና በደማቸው ውስጥ ተለኪያዊ የቫይረስ ቁጥር መጠን የሌላቸውን ግለሰቦች በኤች አይ ቪ ለሌሎች ማስተላለፍ አይችሉም ፡፡ ኤች አይ ቪ እንዲሁ በማኅበራዊ ግንኙነት ማለተም በመሳሳም ፣ በመተቃቀፍ ፣ አንድን ኩባያ በመጋራት ወዘተ ተላላፊ በሽታ አይደለም ፡፡

schedule22.07.2021

→ ኤችአይ ቪ ምንድን ነው?

ኤች አይ ቪ በሽታን የሚከላከልን (immunforsvaret) የሰውነት ስርዓትን የሚያጠቃ ቫይረስ ነው ፡፡ ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሲገባ የሰውነት የበሽታ መከላከያውን ቀስ በቀስ ያዳክማል ወይም ያጠቃል ይህንንም ጥቃት የሚቋቋም መድሃኒት ካልወሰዱ ሰውነትን ለበሽታ እና ለበሽታ መበከል ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋል።

schedule22.07.2021

→ ኤችአየቪ ኖርዌ (HivNorge)

ኤችአቪ ኖርዌ ከኤችአቪ ጋር ለሚኖሩ እና ኑሮአቸውን ኤች አይ ቪ የሚነካ ግለሰቦችን በኖርዌ ውስጥ የሚገኝ ብቸኛ የሆነ የሕሙማን ድርጅት ነው ።እንደዚሁም በተጨማሪም በኤች አይ ቪ ተጠቂ ግለሰቦች ፣ እንዲሁም የፕራይፕ ተጠቃሚዎችን እና በኤች አይ ቪ የምመበከል እድላቸውን ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎች ጨምሮም ላላችው ማንኛውም ለፍላጎታችውም ተቋርቋሪ የፖለቲካ ድርጅትም ነው ፡፡